የተባረከው ረመዳን ወር ድሎች

የተባረከው ረመዳን ወር ድሎች

ረመዳን ከፆም ከቁርኣን ኢባዳነቱ ባለፈ በኢስላም ታሪክ ታላላቅ ዘመቻዎችና መከፈቶች የተደረጉበትም የድል ወር ነው። ከእነዚህም ውስጥ የተወሰኑት የሚከተሉት ናቸው።

♦ ታላቁ የበድር ጦርነት

የበድር ጦርነት የመጀመሪያው የሙስሊሞች ድል ሲሆን የተካሄደው በ2 ሒጅራ ረመዳን 17ኛው ቀን ላይ ነው። ነቢዩ (ዐሰወ) 300 ሰራዊቶችን በመያዝ በሶስት እጥፍ የሚበልጣቸውን የመካ ጣዖታውያን አንገት ያስደፉበት ሲሆን በድር የድሎች ሁሉ አባት ይባላል።

♦ የመካ መከፈት

ነቢዩ (ዐሰወ) ከአስር ዓመታት የመዲና ስደት በኋላ በ11 ሒጅራ ረመዳን 18ኛው ቀን ላይ ከ10 ሺህ የሚበልጥ ሰራዊት በማሰለፍ ወደ ትውልድ ቀያቸው መካ ዘመቱ። የመካ ጣዖታውያንም በሙስሊሞች የደረሰባቸውን ተደጋጋሚ ሽንፈት በማሰብ ካለምንም ጦርነት መካ ተከፈተች።

♦ የአንደሉስ (ስፔን) መከፈት

የዑመዮች ኸሊፋ የጦር መሪ ጣሪቅ ኢብኑ ዚያድ በ92 ሒጅራ ረመዷን 28ኛው ቀን ላይ 12ሺህ የሚሆኑ የሰሜን አፍሪካ በርበሮችንና የተወሰኑ አረቦችን በመያዝ ከ90ሺህ በላይ ሰራዊት ያለውን ንጉስ ሮደሪክ አሸንፎ ስፔንን ከፈተ። ጦርነቱን የረታበት ታላቅ ተራራም በስሙ «ጀበል ጣሪቅ» (ጅብራልተር) ተባለ።

♦ የቁዱስ እንደገና መከፈት

ሰላሑዲን አል-አዩብ በ582 ሒጅራ ረመዷን ወር ላይ ቁዱስን ከመስቀል ጦረኞች ለማስለቀቅ ዘመተ። ከአውሮፓ ከመጡ ስድስት ንጉሶች ጋር ከባድ ውጊያን አድርጎ ፍልስጤምን ነፃ አወጣ። ይህን ታሪካዊ ዘመቻ ብዙ የአውሮፓ ፀሃፍት በሰላሑዲን ጀግንነት በመደነቅ አሞካሽተ
♦  የታታሮች (ሞንጎሎች) መሸነፍ

በ603 ሒጅራ ከምስራቅ ኤዥያ ተነስተው እስከ አውሮፓ ጫፍ ድረስ የዘመቱት ታታሮች በሙስሊሙም ሆነ በሌላው ህዝብ ላይ ከፍተኛ እልቂት ፈፅመዋል። በባግዳድ ብቻ እስከ 200ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል። በ658 ሒጅራ ረመዷን ወር ላይ የመምሉኩ የጦር መሪ ሰይፉዲን ቁቱዝ ባደረገው ዘመቻ ባለ ጠባብ ዓይኖቹ ታታሮች ሊሸነፉ ችለዋል።

እና ረመዳን ሲመጣ እንቅልፍና መኝታ ብቻ ሳይሆን ዘመቻም ነስርም የሚገኝበት የተባረከ ወር መሆኑን እያሰብን ተነቃቅተን ልንፆመው ይገባል።

አላህ በዚህ ወር የምንሰራውን መልካም ስራ ሁሉ ይቀበለን።

Be tacare

ለማሳመን ወስነህ ውይይት አትጀምር ሀሳብ ውስጥ እምነት የለም ሀሳብ ብቻ ነው ያለው። የሀሳብህ ትልቅነት የሚለካው ደግሞ በአቻው ተቃራኒ ሀሳብ የሚወጣው ከሆነ ነው።

እንዲያ ካልሆነ ሀሳብህ ጥግ አይኖረውም ስፍሩን አታቀውም ለውጥ ፈጣሪም አይሆንም። አንተም ቀስ በቀስ ትወዛወዛለህ ቦታህን ትምታታለህ ስለዚህ ጥግ ያለው ሀሳብ ውለድ።

እንዲያ ሲሆን ተቃራኒህም ካንተ እኩል ወይም የላቀ አቅም አስረጂ እንደሚኖረውም ለማመን ትቀርባለህ።

ልብ በል:

ማንም ሀሳብ ሲያወራህ ለማድመጥ ብለህ ስማው። ወረፋ ጠባቂ አትሁን።እስኪጨርስ ብቻ ዝም አትበል እስኪገባህ እንጂ።

thinking
Design a site like this with WordPress.com
Get started